አሐዱ፡ባንክ 2 የዲጂታል መተግበሪያዎችን በይፋ አስመረቀ! Dawit Addis June 19, 2026

አሐዱ፡ባንክ 2 የዲጂታል መተግበሪያዎችን በይፋ አስመረቀ!

ባንካችን “አሐዱ ለኩሉ” እና “ማኅደር” የተሰኙ 2 ዲጂታል መተግበሪያዎችን፤ የአሐዱ፡ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ÷ ከፍተኛ አመራሮች÷ ለመተግበሪያዎቹ መበልጸግ የተሣተፉ ሠራተኞች÷ አጋር ድርጅቶች እና በርካታ የሚዲያ ባለሙያዎች በታደሙበት ሠኔ 11/2018 ዓ.ም. በማርዮት ኤክስክዩቲቭ አፓርትመንትስ በይፋ አስጀምሯል፡፡

የአሐዱ፡ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ፤ አሐዱ፡ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ጉዞውን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ፤ ፕሌይ ስቶር (play store) እና አፕ ስቶር (App store) ላይ በማውረድ ቀለል ባለ ዘዴ መጠቀም የምንችልበት “አሐዱ ለኩሉ” የተሰኘ ዘመናዊ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ እና ለጥቃቅን÷አነስተኛ እና መካከለኛ የንግድ ተቋማት (MSMEs) ያዘጋጀውን፤ እስከ ብር 600,000 ያለምንም ዋስትና ለመበደር የሚያስችል “ማኅደር” የተባለ በገንዘብ ፍሰት ላይ የተመሠረተ የብድር ሥርዓት መተግበሪያ
ማስጀመሩ፤ ባንኩ ለሕዝቡ የገባውን ቃል ተግባራዊ ያደረገበት ዕለት ነው በማለት ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም፤ መተግበሪያዎቹ ሥራ ላይ እንዲውሉ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አጋር ድርጅቶች ማለትም ለ SNV, GIZ, INSA, እና ለባንኩ ሠራተኞች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *