አሐዱ:ባንክ ለ 8ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ! Dawit Addis July 22, 2026

አሐዱ:ባንክ ለ 8ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ!

አሐዱ፡ ባንክ ሥራ የጀመረበትን 4ኛ ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ኩነቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ፤ ከሳሮ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ክቡሩን የሰው ሕይወት ለመታደግ በአያሌው የሚያግዘውን የደም ልገሳ መርሐ-ግብር ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም አካሒዷል፡፡

በዚህም፤ ባንኩ ካሉት ስድስት ዕሴቶች መካከል አንዱ የሆነውን የሰብአዊነት ልዩ ዕሴቱን ተግባር ላይ አውሏል፡፡ የደም ልገሳ መርሐ-ግብሩ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በዛሬው ዕለት ሲከናወን፤ የአሐዱ:ባንክ የሥራ አመራሮች እና ሠራተኞች ደም በመለገስ ተሣትፈውበታል፡፡

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *