
“በክብር እናገለግላለን፤ ከልባችን እናመሰግናለን” በሚል መሪ ቃል የምስጋና ሳምንቱን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ በዛ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡ የምስጋና ሳምንቱ በልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ከዛሬ ታኅሣሥ 20 እስከ ታኅሣሥ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሁሉም ቅርንጫፎች እና በዋናው መሥሪያ ቤት እየተከበረ ይቆያል፡፡ የምስጋና ሳምንቱ ባንኩ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበትንና የምሥረታ ጉባዔ ያካሔደበት ታኅሣሥ 24 አስታኮ የተሰናዳ በመሆኑ፤ ሳምንቱን የበለጠ ደማቅ ያደርገዋል፡፡
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ በዛ፤ “ደንበኞች ለአሐዱ፡ባንክ ቤተሰቦች ናቸውና የአሐዱ ቤተሰብ ሳምንት እያከበርን ነው ብዬ ብገልጸው ለውስጤ ሀሴትን ይሰጠኛል” በማለት በበዓሉ የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የተናገሩት ንግግር፤ ባንካችን የምስጋና ሳምንቱን የሚያከብርበትን መንፈስ በደንብ ያንፀባርቃል፡፡
የምስጋና ሳምንቱ በደንበኞች ተሣትፎ እና የምስጋና መርሐ ግብራት የሚከናወን በመሆኑ፣ ደንበኞች በቅርንጫፎች በመገኘት አብረውን እንዲያከብሩ እንጋብዛለን።