
አሐዱ፡ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋፋት ያለውን መሪ ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፤ ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን የአሐዱ ኢ -ብር ዲጂታል ኤጀንሲ ባንኪንግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የአሐዱ ባንክ የማርኬቲንግና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዐቢይ መልካ እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ቺፍ ኮሜርሺያል ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ ፈርመዋል፡፡ በስምምነቱ ላይ አሐዱ፡ባንክ ከ1,000 በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ቅርንጫፎችን በመጠቀም፤ ዘመናዊነቱ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የአሐዱ ኢ-ብር የዲጅታል የክፍያ አገልግሎትን ለድርጅቱ ደንበኞች በቀላሉ እና በፍጥነት መክፈል የሚያስችላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡ ይህ አገልግሎት፤ ደንበኞች በቀላሉ የአሐዱ ባንክ ሒሳብን ለመክፈት፣ ወጪዎችን ለማዘዝ እንዲሁም ልዩ ልዩ ክፍያዎችን ለመፈጸም የሚያስችል የዲጅታል የክፍያ አማራጭ በመሆን ያገለግላል፡፡ በቀጣይም፤ ኅብረተሰቡን ሊጠቅሙ የሚችሉ ልዩ ልዩ የዲጅታል ቴክኖሎጂ ክፍያ አማራጮችን ለማካተት እንዲሚሠራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
አሐዱ ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች!