
ባንካችን አሐዱ፤ የካቲት 13/2018 ዓ.ም በዳሸን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ለባንኩ የ 30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
ዳሸን ባንክ በ30 ዓመታት ጉዞው ውስጥ ለሀገር እድገት አስተዋፅኦ ያበረከተ እና በርካታ ተቋማትን ሕልማቸው እውን እንዲሆን መርዳት የቻለ ባንክ ነው በማለት የባንካችን ቺፍ ኮርፖሬት ሰርቪስስ ኦፊሰር አቶ ሲሳይ ገብሩ ተናግረዋል፡፡
የዳሸን ባንክ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ አየለ ተሾመ በበኩላቸው፤ አሐዱ፡ባንክ ስሙም ዕሴቶቹም ልቡናን ይማርካሉ፤ በውድድር ሳይሆን በትብብር ለወገንና ለሀገር ለመድረስ በአንድነት እንሠራለን በማለት ገልጸዋል፡፡