አሐዱ:ባንክ በፋይናንስ ተደራሽነት ላይ በተዘጋጀው ሲምፖዚየም ተሣተፈ! Dawit Addis December 18, 2025

አሐዱ:ባንክ በፋይናንስ ተደራሽነት ላይ በተዘጋጀው ሲምፖዚየም ተሣተፈ!

በኤስ ኤን ቪ (SNV) ሊዌይ (LIWAY) ፕሮጀክት አዘጋጅነት፤ ለ “MSMEs የፋይናንስ በሮችን መክፈት፤በኢትዮጵያ በሴቶች÷ወጣቶችና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ያሉ ተግዳሮቶች እና ዕድሎች” በሚል መሪ ሐሳብ፤ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (MSMEs) የፋይናንስ ተደራሽነትን የሚመለከት ታላቅ ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየም ታኅሣሥ 08/2018 ዓ.ም በሃያት ሪጄንሲ ተካሄደ፡፡

ሲምፖዚየሙም ቁልፍ የፋይናንስ ዘርፍ ባለድርሻ አካላትን ማለትም ባንኮችን÷ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን እና ፊንቴክ ኩባንያዎችን በአንድነት በማሰባሰብ የዘርፉን ተግዳሮቶች እና ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ ለመወያየት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ባንካችንም በጥቃቅን÷አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ እና የገጠር ባንኪንግ መምሪያው ያሉትን አገልግሎቶች በማቅረብ እና በማስተዋወቅ ተሣተፊ ሆኗል፡፡

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *