
አሐዱ፡ ባንክ የምሥረታ ጉባዔ በዓሉን በማስመልከት፤ ከሳሮ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ክቡሩን የሰው ሕይወት ለመታደግ በአያሌው የሚያግዘውን የደም ልገሳ መርሐ-ግብር ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም አካሒዷል፡፡ በዚህም ባንኩ ካሉት ስድስት ዕሴቶች አንዱ የሆነውን ሰብአዊነት ተግባር ላይ አውሏል፡፡
የደም ልገሳ መርሐ-ግብሩ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በዛሬው ዕለት ሲከናወን፤ የአሐዱ:ባንክ የሥራ አመራሮች፣ ሠራተኞች እና የሳሮ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን ኃላፊዎች ደም በመለገስ ተሣትፈውበታል፡፡