
ለአሐዱ፡ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች “በሥነ -ምግባራዊ የሥራ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት አስተዳደር “ዙሪያ ከፌዴራል የሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች በድሪም ላይነር ሆቴል ሥልጠናው ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡
የኮሚሽኑ የሥነ-ምግባር እና ፀረ- ሙስና ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ የኋላሸት ደሳለኝ፤ ሥልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ የመንግሥት እና የሕዝብ ተቋማት ላይ አመራር በመሆን የሚያገለግሉ የሥራ ኃላፊዎች በዕለት ከዕለት የሥራ እንቅስቃሴ ወስጥ የሚሰጧቸው የሥራ አመራር ውሳኔዎች ጥራት ያላቸው እና ከጥቅም ግጭት የፀዱ መሆናቸው ከፍ ያለ ተቋማዊ እና ሀገራዊ ፋይዳ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ሥልጠናው በጂማ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁር በሆኑት በዶ/ር እድሪስ የባ የተሰጠ ሲሆን ፤ ሙስናን መዋጋት ለመንግሥት አካላት ብቻ የሚተው ሳይሆን የቤተሰብ ፤ የትምህርት ቤቶች፤ የሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም የሁሉም ማኅበራዊ ተቋማት ኃላፊነት መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል፡፡
በሥልጠናው ላይ የአሐዱ፡ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዩ ልዩ ሐሳቦቸን ያንሸራሸሩ ሲሆን፤ በሥልጠናው መጠናቀቂያ ላይ፤ የአሐዱ፡ ባንክ ቺፍ ኮርፖሬት ሰርቪስስ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሲሳይ ገብሩ፤ ሥልጠናው ለአሐዱ፡ ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ፋይዳው የላቀ መሆኑን ገልጸው ኃላፊዎች ያገኙትን መልካም ተሞክሮ በሥራቸው ለሚገኙ ሠራተኞች በማካፈል ተቋማዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል።