ለጥቃቅን ፣ አነስተኛ እና መካከለኛ የቢዝነስ ተቋማት በዲጂታል እና በፋይናንስ ክህሎት ዙሪያ ላይ ሥልጠና ተሰጠ !! Dawit Addis October 31, 2025

ለጥቃቅን ፣ አነስተኛ እና መካከለኛ የቢዝነስ ተቋማት በዲጂታል እና በፋይናንስ ክህሎት ዙሪያ ላይ ሥልጠና ተሰጠ !!

በአሐዱ፡ባንክ የጥቃቅን ፣ አነስተኛ ፣ መካከለኛ እና የገጠር ባንክ መምሪያ ከተለያዩ የአዲስ አበባና በዙሪያዋ ካሉ አጎራባች ቦታዎች ለመጡ 1000 ለሚሆኑ የጥቃቅን ፣ አነስተኛ እና መካከለኛ የቢዝነስ ተቋማት በዲጂታል እና በፋይናንስ ክህሎት ዙሪያ ላይ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ሥልጠና ተሰጠ ፡፡
በዚህ ሥልጠና ላይ በአሐዱ፡ባንክ የጥቃቅን ፣ አነስተኛ ፣ መካከለኛ እና የገጠር ባንክ መምሪያ ያበለፀገውን “ማኅደር” የተሰኘውን መተግበሪያ ለቢዝነስ ተቋማቱ ያስተዋወቀና ሥልጠና የሰጠ ሲሆን፤ ይህ መተግበሪያ የሒሳብ አያያዝ ችግሮችን የሚቀርፍ ፤ ሙሉ በሙሉ ሽያጫቸውን በየዕለቱ መመዝገብ የሚያስችል ፤ የገንዘብ ፍሰታቸውን ለማስተዳደር እና ለቢዝነስ ውሳኔዎቻቸው የሚያግዝ መተግበሪያ እንደሆነ በሥልጠናው ላይ ተገልጿል ፡፡
በተጨማሪም ይህን መተግበሪያ በመጠቀም የጥቃቅን ፣ አነስተኛ እና መካከለኛ የቢዝነስ ተቋማት እስከ 600,000 ብር ያለምንም ዋስትና መበደር የሚችሉበት መተግበሪያ ሲሆን፤ ይህን ብድርም ለማግኘት ለእነዚህ የቢዝነስ ተቋማት ተብሎ የተዘጋጀውን (MSME Investment account) በመክፈት እና ለሦስት ተከታታይ ወራት መተግበሪያው ላይ የዕለት ተዕለት የቢዝነስ እንቅስቃሴዎችን መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል ፡፡
ይህ መተግበሪያ ለአጠቃቀም ምቹ ሲሆን፤ ከጥቃቅን ፣ አነስተኛ እና መካከለኛ የቢዝነስ ተቋማት ላይ የሚታዩ ችግሮችን የሚቀርፍ ፤ ለሌሎችም የፋይናንስ ተቋማት ምሳሌ መሆን የሚችል እና በዓይነቱ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው እንቅስቃሴ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ተሣታፊዎች አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *