አሐዱ ባንክ የ2018 ዓ.ም የ3ተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አከናወነ Dawit Addis April 21, 2026

አሐዱ ባንክ የ2018 ዓ.ም የ3ተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አከናወነ

የአሐዱ:ባንክ አ.ማ ከፍተኛ ሥራ አመራሮችና የመምሪያ ኃላፊዎች የባንኩን የ 9 ወር ሥራ አፈጻጸም ገምግመዋል፡፡ ሚያዚያ 9/2018 ዓ/ም በኢሊሊ ኢንተርናሸናል ሆቴል ለሙሉ ቀን በተደረገ ስብሰባ በሦስተኛው ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖችንም ሆኑ መሻሻል እንደሚገባቸው የተሰመረባቸው  ጉዳዮች ላይ በስፋት ምክክር ተደርጓል፡፡
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ በዛም በባለፉት ወራት የታዩ ብዙ አበረታች አፈጻጸሞች መኖራቸውን ገልጸው፣ ባንካችን ካለበት ሰፊ ኃላፊነትና ካሉት ዕድሎች አንጻር በትጋት በመሥራት የበጀት ዓመቱን፣ ዕቅዶችን የምናሳካበት አድርጎ ማጠናቀቅ እንደሚቻል በመግለጽ የባንኩን ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ፍላጎት ባማከለ ሁኔታ ውጤታማነትን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባና ሁሉም ኃላፊዎች በውይይቱ የተነሱትን ገንቢ ነጥቦች ወደየሥራ ክፍሎች በማውረድ እንዲተገብሩ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *