በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ላይ የሚገኘው 103ኛው የባንካችን ቅርንጫፍ፤ የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ÷ ሌሎች የቦርድ አባላት÷የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ በዛ÷የባንካችን ከፍተኛ የሥራ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በታደሙበት፤ በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አባቶች ጸሎት እና ቡራኬ ተመርቆ መስከረም 03/2018 ዓ.ም በይፋ ሥራ ጀመረ::
በዕለቱም የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ፤ ቅርንጫፎችን እንዲህ የምንከፍተው ኢትዮጵያውያንን/ትን በክብር ለማገልገልና ነውና ሁላችንም ሒሳብ በመክፈት እና አክሲዮን በመግዛት እንገልገልበት ብለዋል::
የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ በዛ በበኩላቸው፤ ከብዙዎች ለብዙዎች በሚል መርሕ ተግባሩን እየከወነ የሚገኘው ባንካችን ለብዙዎች ለመድረስ እየተጋ በመሆኑ፤ በትብብር በመሥራት ባንካችንን ወደ ሚፈለገው ውጤት ማድረስ ይጠበቅብናል በማለት ተናግረዋል::