አሐዱ፡ባንክ በንግድና ፋይናንስ ፎረም ላይ ተሣተፈ! Dawit Addis December 10, 2025

አሐዱ፡ባንክ በንግድና ፋይናንስ ፎረም ላይ ተሣተፈ!

በ GIZ Ethiopia እና KFW Development Bank አዘጋጅነት፤ “Firm and Finance ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሐሳብ 170 ኩባንያዎች÷የፋይናንስ ተቋማት÷የኢንቨስትመንት አማካሪዎች እና የልማት አጋሮች በታደሙበት፤ የንግድ እና የፋይናንስ ፎረም ኅዳር 29/2018 ዓ.ም በጋላኒ ሮስተሪ ተካሒዷል፡፡

ፎረሙም ለተወዳዳሪ እና ወደ እድገት ጎዳና ለሚገሠግሡ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሻሻል የተዘጋጀ ከፍተኛ የንግድ እና የፋይናንስ መድረክ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የኩባንያዎች አቅምን ከፋይናንስ መፍትሔዎች ጋር በተግባር ለማገናኘት የተዋቀረ የመግባባት እና የእርምጃ መድረክ እንደነበረም ለመረዳት ችለናል፡፡

ባንካችንም በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ እና የገጠር ባንኪንግ መምሪያው ያሉትን አገልግሎቶች በማቅረብ እና በማስተዋወቅ መልካም ግንኙነትን ፈጥሮበታል፡፡