አሐዱ፡ባንክ 5ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን በስኬት አጠናቀቀ! ከታክስ ክፍያ በፊትም ብር 1.07 ቢሊዮን ትርፍ አስመዘገበ! በአንድ አክሲዮን የተገኘው የትርፍ መጠንም (Earning per share) 65 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።  Dawit Addis November 11, 2026

አሐዱ፡ባንክ 5ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን በስኬት አጠናቀቀ! ከታክስ ክፍያ በፊትም ብር 1.07 ቢሊዮን ትርፍ አስመዘገበ! በአንድ አክሲዮን የተገኘው የትርፍ መጠንም (Earning per share) 65 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። 

አሐዱ፡ባንክ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በወሳኝ መለኪያዎች አመርቂ ውጤት አስመዘገበ፡፡ በሒሳብ ዓመቱ፤ የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 10.47 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ33 በመቶ እድገት ዐሳይቷል፡፡
በውጭ ምንዛሬ ግኝት ረገድም ከ121.3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፤ ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ38 በመቶ እድገት አስመዝግቧል፡፡ በተመሳሳይ፤ የባንኩ ጠቅላላ ገቢ ከብር 3.2 ቢሊዮን ብር በላይ በመሆን፤ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ48 በመቶ እድገት አስመዝግቧል፤ አጠቃላይ ሀብቱንም ብር 14.32 ቢሊዮን ብር በላይ በማድረስ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ42.5 በመቶ እድገት በማስመዝገብ ከፍተኛ እመርታን ዐሳይቷል፡፡  በመሆኑም፤ በ2025/26 ሒሳብ ዓመት ባንኩ አመርቂ አፈጻጸም በማሳየት፤ ከታክስ ክፍያ በፊት ብር 1.07 ቢሊዮን ትርፍ አስመዝግቧል፤  ከ2024/25 ሒሳብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ113.1 በመቶ ብልጫ ያለው የትርፍ እድገት ዐሳይቷል፡፡
የአሐዱ፡ባንክን የወደፊት ጉዞ የሚቀርፁ፣ ስትራቴጂካዊ ፋይዳቸው የገዘፈ ሁለት ዐበይት ስኬቶችንም ዕውን አድርጓል፡፡ የመጀመሪያው፤ ባንኩ ከመሬት በታች 2፣ ባለ ወለል እና 15 ከመሬት በላይ ፎቆች (2B+G+15) ያሉትን የራሱን ግዙፍ የንግድ ሕንጻ በመግዛት የረጅም ጊዜ ርዕዩን እንዲሁም በወደፊት እድገቱ እና ዘላቂነቱ ላይ ያለውን መተማመን ያሳየበት ጭምር ነው፡፡

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *