ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ! Esubalew D October 19, 2023

ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ!

አሐዱ ባንክ ለደንበኞቹ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ዘመኑን ከዋጁ አዳዲስ ምርቶቹ ውስጥ አንዱ የሆነውን ኮርፖሬት ዴቢት ካርድ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ በየትኛውም ካርድ ማግኘት የማይችሉትን በዓይነቱ ልዩ የሆነ አገልግሎት በቀን እስከ 25,000.00 ብር ካሽ ማውጣት ያስችልዎታል ፡፡ እንዲሁም በማንኛውም የፖስ (POS) ማሽን በመጠቀም በቀን እስከ 100,000.00 ብር ግብይትዎን መፈጸም ያስችልዎታል፡፡  አገልግሎቱን በሁሉም ባንኮች ኤቲኤም(ATM) እና ፖስ (POS) ማግኘት ይችላሉ፡፡ በተያያዘም የባንካችን ATM ማሽን ሥራ መጀመሩን እያበሠርንዎ በማንኛውም ATM ካርድ ወጪ ማድረግ እንደሚችሉ  ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው።