ጉባኤው ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እንደ መሆኑ መጠን፤ ለውይይት የያዛቸው አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ጉባዔውን አጠናቋል፡፡
ይኽ በእንዲህ እንዳለ፤ ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት (እ.ኤ.አ. 2024/25) አመርቂ አፈጻጸም አሳይቷል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
- ከብር 2.1 ቢሊዮን በላይ ገቢ በመሰብሰብ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት የብር 1 ቢሊዮን ጭማሪ ወይንም 90.9 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡
- የእርጅና ተቀናሽን ጨምሮ ከተያያዥ ወጪዎች በኋላ እንዲሁም ከመጠባበቂያና ግብር በፊት ብር 569 ሚሊዮን ያተረፈ ሲሆን፤ ይኽም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት የብር 450 ሚሊዮን ብልጫ ወይም 278.1 በመቶ እድገት አስመዝግቧል፡፡
- የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 7.8 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ይኽም ከባለፈው በጀት ዓመት አንጻር የ68 በመቶ እድገት አስመዝግቧል፡፡
- በውጭ ምንዛሬ ገቢ ረገድ ከUSD 88 ሚሊዮን በላይ መሰብሰብ ተችሏል፡፡
- አጠቃላይ ሀብቱም የ57 በመቶ እድገት በማስመዝገብ ከብር 10 ቢሊዮን በላይ በማድረስ ከፍተኛ ዕመርታን አሳይቷል፡፡
- የደንበኞቹን ቁጥር ከ1 ሚሊዮን በላይ አድርሷል፡፡
በአጠቃላይ፤ አሐዱ፡ባንክ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 የተጠናቀቀውን የ2024/25 የበጀት ዓመት በአንፀባራቂ ስኬቶች ታጅቦ ማጠናቀቁን ስናበሥር ታላቅ ደስታ ይሰማናል፡፡
ለዚህ ስኬት የጎላ አስተዋፅኦ ላደረጋችሁልን ክቡራን/ት ደንበኞቻችን፣ ባለአክሲዮኖቻችን፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድና የሥራ አመራር አባላት፣ ሠራተኞቻችን እንዲሁም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት እያመሰገንን፤ በአዲሱ በጀት ዓመት ጠንክረን በመሥራት ከዚህ የላቀ ስኬት የምናስመዘግብበት እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለን፡፡