እነሆ ደስ የሚያሰኝ መልካም ዜና ከአሐዱ ባንክ!አሐዱ፡ባንክ “በ 1 ቅርንጫፍ 1 ልጅ” መልካም ተግባርን አስቀጠለ! Dawit Addis January 9, 2026

እነሆ ደስ የሚያሰኝ መልካም ዜና ከአሐዱ ባንክ!አሐዱ፡ባንክ “በ 1 ቅርንጫፍ 1 ልጅ” መልካም ተግባርን አስቀጠለ!

ለወገንና ለሀገር መድረስን በርዕይ የሰነቀው አሐዱ፡ባንክ ታኅሣሥ 24 የሚያከብረውን የምሥረታ ጉባዔ በዓሉን በማስመልከት፤ ባሉት ቅርንጫፎች ቁጥር ልክ ድጋፍ/እርዳታ የሚሹ ”ሕፃናትን በማደጎ በመረከብ” ለማሳደግ ፈቃደኛ መሆኑን በዋና ሥራ አስፈጻሚው በአቶ ሙሉጌታ በዛ በኩል አሳወቀ፡፡
አቶ ሙሉጌታ በዛ በንግግራቸው፤ ባንኩ እና ሠራተኞቹ የተወሰኑ ሕፃናትን ባለፉት ሦስት ዓመታት በቅርንጫፎቹ በኩል ሲደግፉ/ሲረዱ ቢቆዩም፤ አሁን ግን ባሉት ቅርንጫፎች ቁጥር ልክ ድጋፍ/እርዳታ የሚሹ ልጆችን በቋሚነት እየደገፉ ለመቀጠል ከገብር ኄር የጤና እና ማኅበራዊ ልማት በጎ አድራጎት እና አቡነ ዜና ማርቆስ የሕፃናትና አረጋውያን መርጃ ማኅበራት ጋር ይህን በጎ ተግባር ለማስቀጠል ፈቃደኛ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡
አንድ ቅርንጫፍ ለአንድ ልጅ! የሚለው ባንኩ ሥራ በጀመረበት ዓመት በቦርድ ዳይሬክተራችን አቶ አንተነህ ሰብስቤ ይተገበራል ብለው ለሕዝብ የገቡት ቃል ኪዳን ሲሆን፤ ባንኩ አንድ ቅርንጫፍ በከፈተ ቁጥር ድጋፍ/እርዳታ የሚሹ ”ሕፃናትን በማደጎ ተረክቦ” በማሳደግ ሰብአዊነት የሚለውን ዕሤቱን ወደ መሬት ከሚያወርድባቸው ተግባራት አንዱ ነው፡፡
አንድ ቅርንጫፍ ለአንድ ልጅ!

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *